ሦስት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የዙምባብዌ ፕሪሚየር ሊግ ወሳኝ ጨዋታዎችን ይመራሉ
የዙምባቡዌ ፕሪሚየር ሊግ ሊጠናቀቅ የሦስት ጨዋታዎች ዕድሜ ብቻ የሚቀሩት ሲሆን ሊጉንም ሀርድ ሮክ በ70 ነጥቦች ሲመራው ስኮትላንድ ኤፍ ሲ ደግሞ በሁለት ነጥቦች ዝቅ ብሎ በ68 ነጥቦች ይከተላል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

አስራ ስምንት ክለቦች በሚካፈሉበት እና የ34ኛ ሳምንቱ ላይ በደረሰው የሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን እጅግ ተጠባቂ ሁለት መርሀግብሮች ዛሬ በተመሳሳይ ሰዓት ሲደረጉ ሦስት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች እነኚህን ጨዋታዎች እንዲመሩ መመረጣቸውን ሀገሬ ቴሌቪዥን ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።
ሊጉን በ36 ጎሎች እና በ70 ነጥቦች እየመራ የሚገኘው ሀርድ ሮክ በሜዳው ፕላቲኒየም ክለብን ሲያስተናግድ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ ከረዳት ኢንተርናሽናል ዳኛ ፋሲካ የኋላሸት ጋር በዋና እና በረዳት ዳኝነት ከሀገሪቱ ሁለት ተጨማሪ ዳኞች ጋር በጋራ ሲመሩ በ39 ጎሎች እና በ68 ነጥቦች ሁለተኛ ላይ የተቀመጠው ስኮትላንድ ኤፍ ሲ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ትሪያንግል ዩናይትድን ሲገጥም ይህንን ጨዋታ ደግሞ ከሀገሪቱ ሦስት ዳኞች ጋር በጋራ በመሆን ኢንተርናሽናል ዳኛ ትግል ግዛው ይመራዋል።
ሁለቱም ጨዋታዎች ዘጠኝ ሰዓት ሲል በተመሳሳይ ሰዓት የምክጀመሩ ይሆናል።
