የ2019 የሕፃናት ሩጫ በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበው ውድድር ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎች ተሳተፉ
በ2019 የሕፃናት ሩጫ በባንክ ኦፍ አሜሪካ በቀረበው ውድድር ላይ ዕድሜያቸው ከ4 እስከ 11 ዓመት የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት በመሳተፋቸው፣ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዛሬ ማለዳ ደምቆ አርፍዷል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

ውድድሩ በሦስት የዕድሜ ምድቦች ማለትም ከ5፣ ከ8 እና ከ11 ዓመት በታች ተሳታፊዎችን ያስተናገደ ሲሆን፤ በውድድሩ ታሪክ ከፍተኛው የሆነው የ5,000 ተሳታፊዎች ምዝገባ በመመዝገቡ፣ ይህንን ከፍተኛ ቁጥር ለማስተናገድ ውድድሮቹ ከሁለት የተለያዩ መነሻ ቦታዎች ተጀምረዋል።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መሥራች ኃይሌ ገብረሥላሴ በውድድሩ ላይ በመገኘት፣ ከሩጫው ቀደም ብሎ በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋዊ አቀባበል ከተደረገላት ኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቼቤት ጋር በመሆን ለሕፃናቱ ሽልማቶችን አበርክተዋል።
ውድድሩም ማየት የተሳናቸው፣ አካል ጉዳተኛ የሆኑ እና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ሕፃናት ሩጫዎችን በማካተት ተጀምሯል። ይህ የሩጫ ውድድር «ውሃን እንንከባከብ ፤ የልጆች ነገን እንጠብቅ።» በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል።
