ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የነርቭ ሕመሞች ሕክምና መመሪያ ይፋ አደረገች

የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የነርቭ ሐኪሞች ማኅበር፣ ከኢትዮጵያ የሥነ-አእምሮ ማኅበር እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን የመጀመሪያውን ሀገር አቀፍ የነርቭ ሕመሞች ሕክምና መመሪያ ይፋ አደረገ።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

መመሪያው በዋናነት እንደ ስትሮክና የሚጥል በሽታ ያሉ የነርቭ ሕመሞችን በመጀመሪያ ደረጃ የጤና ተቋማት በማስረጃ ላይ ተመሥርቶ ለመለየት፣ የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና ለመስጠትና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ወደ ከፍተኛ ሕክምና ተቋማት ሪፈር ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

በጤና ሚኒስቴር የተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች (NCDs) ዴስክ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት አየለ እንደገለጹት መመሪያው የነርቭ ሕክምናን ከሪፈራል ሆስፒታሎች ባሻገር በገጠርና በሩቅ አካባቢዎች ተደራሽ በማድረግ የሕክምና ጥራትና ፍትሐዊነትን ለማሻሻል ከፍተኛ ፋይዳ አለው።

ለመመሪያው ስኬታማነትም የጤና ባለሙያዎችን አቅም እስከ ታችኛው እርከን ማጠናከር፣ የመድኃኒት አቅርቦትን ማሻሻል፣ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ፣ ጠንካራ የሪፈራል ሥርዓት መዘርጋትና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እንደሚገባ ተመላክቷል።

ይህ መመሪያ ማንኛውም ዜጋ በነርቭ ሕመም ምክንያት ከተገቢው እንክብካቤ እንዳይገለል በማድረግ ፍትሐዊና ሁሉን አቀፍ የጤና ሥርዓት ለመገንባት የተወሰደ ወሳኝ እርምጃ መሆኑ ተጠቁሟል።

አጋራ

YouTube

አማEN