ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

በቦልተን 4 ለ 0 የተሸነፉት የቀድሞው የዩናይትድ አሰልጣኝና ፖቸቲኖ ከ100 ዓመት በኋላ

"ጠዋት ከስራህ ትባረራለህ" የሊቨርፑል ደጋፊዎች የምንጊዜም ተቀናቃኛቸውን ማንችስተር ዩናይትድን በሜዳቸው 4 ለ 0 ካሸነፉ በኋላ ለማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ያስተላለፉት መልዕክት ነበር።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኝው ማንችስተር ዩናይትድን 19ኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ ያስገደደው ውጤት የተመዘገበው በአንፊልድ በሊቨርፑል 4 ለ 0 መሸነፉን ተከትሎ ነው።

ሌኒ ዮሮን 8ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ያጡት ቀያይ ሰይጣናቱ 90 ደቂቃው አላልቅላቸው ብሎ አምሽተዋል።

ባሳለፍነው ረቡ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድንን እየመሩ ሄይቲን ካሸነፉ በኋላ 3800 ማይል ተጉዘው ማንችስተር የደረሱት አዲሱ አለቃ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በአንፊልድ የአሰልጣኞች መቆሚያ ቦታ ላይ ሆነው ቡድናቸውን ገና በስርዓት መምራት ሳይጀምሩ በሌኒ ዮሮ ድንገተኛ ቀይ ካርድ ምክንያት ስለሚቀይሩት ተጨዋች እና ሰለሚገጥማቸው ፈተና ለመጨነቅም ተገደዋል።

ወትሮም ቢሆን በአንፊልድ ጥሩ ታሪክ የሌላቸው ሰው ፖቸቲኖ በመጀመሪያ ጨዋታቸው 4 ግቦች ተቆጥረውባቸው በድንጋጤ ከመርሲሳይድ ውጥተዋል።

የመጨረሻው ፊሽካ እስኪነፋ በደስታ የሰከሩት የሊቨርፑል ደጋፊዎች ስለ ፖቼቲኖ ወዲያውኑ መባረር እና ስለ ዩናይትድ ወደ ታችኛው ሊግ መውረድ እየዘመሩ አምሽተዋል።

ደጋፊዎቹ ፖቸተኒኖ ዩናይትድን ወደ ታችኛው የሊግ እረክን የሚወሰደውን መኪና መሪውን ይዟል በማለት የተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎችን ለማበሳጨት ሲሞክሩም ታይተዋል።

ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን በኋላ የዩናይትድ 12ኛው አሰልጣኝ ሆነው ኦልድትራፊርድ የደረሱት አርጀንቲናዊው ሰው ከ100 ዓመት በኋላ ሊታወስ የማይፈለገውን ታሪክ የተጋሩበትም ሆኗል።

ልክ ከ100 ዓመት በፊት በ1926 ሂልዲች ማንችስተር ዩናይትድን ከተረከቡ በኋላ በመጀመሪያ ጨዋታቸው በቦልተን 4 ለ 0 የተሸነፉ ሲሆን ሰውየው ከ30 ጨዋታዎች በኋላ ድጋሜ ወደ አሰልጣኝነት አልተመለሱም።

ከሊጉ መሪ አርሰናልን በ20 ነጥብ ርቆ የተቀመጠው ዩናይትድ በ12ኛ ሳምንት መርሀግብር ከብሬንትፊርድ የሚገናኝ ይሆናል።

አጋራ

YouTube

አማEN