ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

“የቡድኑ አቋም እና የደጋፊዎች አጸፋዊ ምላሽ ተቀባይነት የለውም” ሮይ ኪን

ማንችስተር ዩናይትድ በአዲሱ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ስር የመጀመሪያ ጨዋታውን በአንፊልድ ከሊቨርፑል ጋር አድርጎ 4 ለ 0 በሆነ ከባድ ውጤት ከተሸነፉ በኋላ በርካታ ሀሳቦች እየተሰነዘሩ ይገኛል፡፡

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ጨዋታውን ተከትሎ የቀድሞው የክለቡ አምበል ሮይ ኪን የተጫዋቾቹን ኃላፊነት የጎደለው አጨራረስ እና ከጨዋታው በኋላ ያጨበጨቡትን ተጓዥ ደጋፊዎች በጠንካራ ቃላት ወቅሷል።
ጨዋታው በተጀመረ በስምንተኛው ደቂቃ ተከላካዩ ሌኒ ዮሮ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውታቱ ለማንችስተር ዩናይትድ ትልቅ ፈተና ሆኗል።

በ13ኛው ደቂቃ ውስጥ ዶሚኒክ ስዞቦዝላይ በቅጣት ምት እና ፍሎሪያን ዊርትዝ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሊቨርፑል 2 ለ 0 ሲመራ፣ በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ ሪዮ ንጉሞሃ እና ቪክቶር ሙኖዝ ሌሎች ሁለት ግቦችን አክለው ውጤቱን 4 ለ 0 መጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡

ከጨዋታው በኋላ ለስካይ ስፖርት ሃሳቡን የሰጡት ሮይ ኪን፤ ደጋፊዎች ለተጫዋቾቹ ያጨበጨቡት ለምንድነው? ጥሩ ላልሆነ አጨዋወት ነው የሚያጨበጭቡት? ሲል በብስጭት ተናግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ በ11 የሊግ ጨዋታዎች አንድ ድል ብቻ በማስመዝገብ በወራጅ ቀጠና ውስጥ መቆየቱን ያነሳው ኪን፤ ሊቨርፑል ስምንት ወይም ዘጠኝ ግቦችን ማስቆጠር ይችል እንደነበር እና የ4 ለ 0 ሽንፈት ተቀባይነት እንደሌለው አስገንዝቧል።

አጋራ

YouTube

አማEN