ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

በ 14 ዓመት 25 አሠልጣኞችን ያሰናበተው የፖዞ ቤተሰብ!

የእንግሊዝ ክለብ ዋትፎርድ በሼፍልድ ዩናይትድ ከተሸነፈ በኋላ ጣሊያናዊውን አሠልጣኝ አሌሲዮ ዲዮኒሲን አሰናብቷል።

ዜና ክፍል · · 2 ደቂቃ ንባብ

ዋትፎርድ በጣሊያናዊያኑ የፖዞ ቤተሰቦች መተዳደር የጀመረው ከ 14 ዓመታት በፊት ሲሆን በነዚህ ጊዜያት ውስጥ 25 አሠልጣኞችን አሰናብቷል።

26ኛ አሠልጣኝ ለመቅጠር ጥረት ላይ የሚገኘው ክለቡ ለአንድ አሠልጣኝ የሚሰጠው ጊዜ በአማካይ 210 ቀናቶች ብቻ ናቸው።

የፖዞ ቤተሰቦች ከፈረንጆቹ ሰኔ 29/2012 ጀምሮ ዋትፎርድን ከመረከባቸው ባለፈ በሀገራቸው ጣሊያን ኡዴኔዜን ከ 1986 ጀምሮ እያስተዳደሩ ይገኛሉ።

ፕሬዝዳንቱ ጂኖ ፖዞ ትልቅ ተስፋ የሚጣልባቸውን ተጨዋቾች በዝቅተኛ ገንዘብ በማስፈረም በውድ ዋጋ በመሸጥ ይታወቃሉ ለዚህ እንደ ማሳያ የሚወሰዱት ብራዚላዊያኑ ሪቻርልሰን እና ጆኣኦ ፔድሮ ናቸው።

በፖዞ ቤተሰብ የመጀመሪያ ሰባት ዓመታት ክለቡ አስከፊ ከሆነ ችግር ውስጥ ወጥቶ ለኤፍ ኤ ካፕ ፍፃሜ እስከመጫወት ደርሷል።

ዋትፎርድ በስፔናዊው አሠልጣኝ ዣቪ ጋርሲያ እተመራ በ 2019 በማንችስተር ሲቲ ተሸንፎ የኤፍ ኤ ካፕን ያጣ ሲሆን በአውሮፓ ውድድሮች ለመሳተፍ እጅጉን ተቃርቦ ነበር።

ከዚያ በኋላ ግን ዋትፎርድን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዳግም የተመለከትነው አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በሻምፒዮንሺፑም ባለፈው የውድድር ዘመን 16ኛ ደረጃን ይዞ ነው ያጠናቀቀው።

በአዲሱ የውድድር ዘመን ለዋትፎርድ ጥሩ አይመስልም ከ 16 ጨዋታዎች በኋላ 15 ነጥብ ይዘው 21ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በእንግሊዝ የጂኖ ፖዞ አስተዳደራዊ መዋቅር በበዙት የአሠልጣኝ ሹም ሽሮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተወቀሰ ቢገኝም በሀገራቸው ጣሊያን ግን ልክ እንደ ልዩ ሀሳብ አመንጪ ተደርገው ይወሰዳሉ።

ወጣቶችን መልምሎ በመግዛት በከፍተኛ ገንዘብ መሸጥ ለኡዴኔዜ አዋጭ መንገድ እንደሆነ ይታመናል። እንደ ዜሌንስኪ ፣ አሌክሲስ ሳንቼዝ ፣ ሮድሪጎ ዴ ፓውል ፣ አሌክስ ሜሬት እና ዩዋን ኩዋድራዶ ያሉ ኮኮቦች በፖዞ ድንቅ መንገድ የተገኙ ናቸው።

አጋራ

YouTube

አማEN