ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ፖቼቲኖ ዋጋ የከፈሉበት ማቲያስ ዴሊክት!

አርጀንቲናዊው አሠልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ በማንችስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ ጨዋታቸው ማቲያስ ዴሊክትን ቋሚ ማድረጋቸው በብዙ ለመተቸታቸው ምክንያት ሆኗል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ፖቼቲኖ ለረዥም ጊዜ ሲመኙት የነበሩትን ክለብ ማሠልጠን የፈጠረባቸው ደስታ ለረዥም ደቂቃዎች የዘለቀ አልነበረም በ15 ደቂቃ ውስጥ በ2026 ማንችስተር ዩናይትድን የማሰልጠን አስከፊ እውነታ ለመጋፈጥ ተገደዋል።

አዲሱ አሰልጣኝ ማቲያስ ዴሊክት በካሪንግተን በነበሩ ሶስት የልምምድ ክፍለ ጊዜዎች ባሳየው እንቅስቃሴ በ357 ቀናት ውስጥ የመጀመሪያውን የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በቋሚ አሰላለፍ እንዲጀምር መወሰናቸው ትልቁ ስህተታቸው ሆኖ ተቀምጧል።

​ኔዘርላንዳዊው ተከላካይ ባለፈው የውድድር ዘመን ህዳር 30 ባስተናገደው የጀርባ ጉዳት እንቅስቃሴው እስኪገደብ ድረስ በፕሪሚየር ሊጉ እያንዳንዱን ደቂቃ በተጫወተበት ወቅት ምናልባትም የዩናይትድ ምርጥ ተጫዋች ነበር።

ነገር ግን ከወራቶች በፊት ማይክል ካሪክ በተከላካይ ክፍሉ መሳሳት ምክንያት ማቲያስ ዴሊትን በኮሞ ጨዋታ ለመጠቀም ከወሰነ በኋላ የጣሊያኑ ጨዋታ ተጨዋቹ ያለበት ወቅታዊ ብቃት በግልፅ የሚታይ ነበር።

ዴሊት ለስድስት ሳምንታት ሙሉ ልምምድ ቢሰራም ለረዥም ጊዜ ከሜዳ መራቁ በሜዳ ላይ ያለው የጨዋታ ዝግጁነቱን በቀጥተኛነት ጎድቶታል።

የአንፊልዱ ጨዋታ ከተጀመረ በኋላ በነበሩት የመጀመሪያ ደቂቃዎች ማቲያስ ዴሊት የሰራው የአቋቋም ስህተት እና የትኩረት ማጣት የቡድኑ አጋሩ ሌኒ ዮሮ ለተጨማሪ ስህተት እንዲዳረግ እና ከሜዳ በቀይ ካርድ እንዲወጣ ትልቁ ምክንያት ነበር።

ማንችስተር ዩናይትድ ለተቆጠረበት አራተኛው ጎልም መነሻው ላይ ትልቁን ስህተት የሰራው እራሱ ማቲያስ ዴሊት ነበር። በተለይም ለዜርክዚ ለማቀበል የሞከረው ኳስ ከአደጋ ቀጠናው የራቀ ባለመሆኑ ቨርጅል ቫን ዳይክ ጫና በማሳደር ኳሱን መንጠቅ እንዲችል አድርጎታል።

ማንችስተር ዩናይትድ የተሸነፈው እንደ ቡድን ጥሩ ባለመሆኑ ቢሆንም ማቲያስ ዴሊትን በቋሚነት ማስጀመራቸው ግን ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን በግልፅ ዋጋ አስከፍሏቸዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN