“በማንቸስተር አንድ ክለብ ብቻ ነው ያለው እሱም ማንቸስተር ዩናይትድ ነው” ራስመስ ሆይሉንድ
ምሽት በኢትሀድ በተደረገው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 5ኛ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ከ ናፖሊ ሁለት አቻ ተለያይተዋል። የጨዋታውን ቀዳሚ ግብ ያስቆጠረው ደግሞ የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ ራስመስ ሆይሉንድ ነው።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1
ዴንማርካዊው አጥቂ ግብ ካስቆጠረ በኋላ ለማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች ያስተላለፈው መልዕክት አነጋጋሪ ሆኗል። ሆይሉንድ በአንድ ጣቱ እያመለከት በማንቸስተር አንድ ክለብ ብቻ ነው ያለው እሱም ማንቸስተር ዩናይትድ ነው በማለት ለቀድሞ ክለቡ ያለውን ክብር ገልጿል።
ሆይሉንድ ከአታላንታ በ72 ሚሊዮን ፓውንድ ዩናይትድን ከተቀላቀል በኋላ በማንቸስተር ዩናይትድ በነበረው የሦስት ዓመት ቆይታ ራሱን ማሳየት ባለመቻሉ ነበር ወደ ሌላኛው የጣልያን ክለብ ናፖሊ ያመራው።
ባናፖሊ ድንቅ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው ወጣቱ አጥቂ ምንም እንኳን ከዩናይትድ ቢለያይም አሁንም ዩናይትድ በልቡ ውስጥ እንዳለ አሳይቷል።
ከጨዋታው በኋላም ለቲኤንቲ ስፖርት በሰጠው ሀሳብ በማንቸስተር ሲቲ እና በዩናይትድ መካከል የቆየ ባላንጣነት አለ እኔ ደግሞ ከዩናይትድ ጋር ያሳለፍኩት ታሪክ ያለኝ በመሆኑ ደስታየን በዚህ መልኩ ለገልጽ ችያለሁ ብሏል።
