ኢንዞ ማሬስካ እና እየሰሩ ያልሆኑ መፍትሄዎቻቸው!
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 2
ግን በተለያዩ ጊዜያት ከመገናኛ ብዙኃን ጋር በሚያደርጋቸው ቃለ-መጠይቆች በተለያዩ ቦታዎች ትክክለኛ መፍትሔዎችን ለማግኘት እየሞከሩ መሆኑን ይገልፃሉ።
ባለፈው ቅዳሜ ከፉልሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ አዩብ ቡአዲን እና ኤሊዮት አንደርሰንን በመሃል ሜዳ ስለ-ማጣመራቸው ሲናገሩ “ይህ ለእኛ ሌላ መፍትሔ ነው። በዚህ ወቅት ከተጨዋቾቻችን ጋር እርስ በርስ ይበልጥ ለመተዋወቅ እንዲሁም ትክክለኛውን መፍትሔ ለማግኘት እየሞከርን ነው ” ብለው ነበር።
ኢንዞ ማሬስካ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ አስተያየት እየሰጡ የሚገኙት አሁን ላይ ቡድኑ የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ላይ በመሆኑ እና ነገሮች ተቀናጅተው ወደ ትክክለኛው መስመር ለመምጣት ጊዜ እንደሚወስዱ ለማስረዳት እንዲረዳቸው ይመስላል።
በህዳር ወር መጀመሪያ ላይ እና ከዚያም በኋላ በነበራቸው አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ”አሁን አብረን መስራት ከጀመርን ሦስት አራት ወራት ሆኖናል እነሱ እኔን ማወቅ አለባቸው እኔም እነሱን ማወቅ አለብኝ” ሲሉ ተናግረው ነበር።
አሠልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ወደ አለም አቀፍ እረፍት ከማምራታቸው በፊት ማንችስተር ሲቲ በተከታታይ ሶስት የሊግ ጨዋታዎች መሸነፉን ተከትሎ የአማካይ ክፍላቸው ላይ አንዳንድ የለውጥ ሙከራዎችን ለማድረግ ተገደው ታይተዋል።
የሲቲ መሃል ሜዳ በእጅጉ የተሻሻለ ቢመስልም ጨዋታዎችን በሙሉ ብልጫ ለማሸነፍ ግን በቂ አልነበረም ምክንያቱም በአጠቃላይ ጉልበት አንሷቸው እና ዝግ ብለው ይታዩ ነበር።
በተለይም ኳሱን ከኋላ መስርተው የሚወጡበት እና ተጋጣሚ ላይ ጫና የሚያሳድሩበት መንገድ የተደራጀ አይደለም።
ማንችስተር ሲቲ ያለፉትን አምስት ጨዋታዎች በሁሉም ውድድር ማሸነፍ ተስኖት ችግሮቹንም ሙሉ ለሙሉ ሳይቀርፍ በመጪው እሁድ የሊጉን መሪ አርሰናል በኤምሬትስ ይገጥማሉ።
