ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ከአፍሪካ ስፔሻል ኦሊምፒክስ ጋር ተወያየ

የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎች በስፖርት የሚኖራቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፣ በአፍሪካ ስፔሻል ኦሊምፒክስ እና በኢትዮጵያ ስፔሻል ኦሊምፒክ ኮሚቴ መካከል ተካሂዷል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ መኪዩ መሀመድ ስፖርት ለሁሉም የሚለውን መርህ መሠረት በማድረግ ሁሉም ዜጎች ከስፖርት እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የመንግሥት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

ስፖርት ብሔራዊ አጀንዳ በመሆኑ በስፖርት መሠረተ ልማት ላይ በስፋት እየተሠራ እንደሆነ የገለጹት አቶ መኪዩ መሀመድ ከአፍሪካ ስፔሻል ኦሊምፒክስ ጋር በትብብር ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነትም አረጋግጠዋል።

የአፍሪካ የስፖርት ተቋማት መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ እንዲያደርጉም በጥናት ላይ የተመሠረተ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ሚኒስቴር ዴኤታው ተናግረዋል።

የአፍሪካ ስፔሻል ኦሊምፒክስ ፕሬዝዳንትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቻርልስ ናያምቤ በአፍሪካ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ዜጎች በስፖርት ለማሳተፍ ከመንግሥታት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ አፍሪካውያንን የሚያስተሳስር የአየር መንገድ ባለቤት መሆኗም በአገሪቱ በስፔሻል ኦሊምፒክስ ላይ በትኩረት በመሥራት ውጤት ለማምጣት እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

የአፍሪካ ስፔሻል ኦሊምፒክስ ለኢትዮጵያ ስፔሻል ኦሊምፒክ ኮሚቴ የገንዘብና የሥልጠና ድጋፍ እንደሚያደርግም ፕሬዝደንቱ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ስፔሻል ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት ኢንጅነር ግርማ ዘውዱ የዛሬው ውይይት በሀገራችን የጀመርነውን የእዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ዜጎች በስፖርት የማሳትፍ ተግባር ይበልጥ የምናጠናክርብት እና የገጠመንን የግንዘብ ችግር በተወሰን መልኩ የምንቀርፍበት ይሆናል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ከ3 ሚሊዮን በላይ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎች እንደሚገኙ በነበረው ውይይት ላይ ተጠቅሷል።

አጋራ

YouTube

አማEN