ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የአውሮፓ ሊግ አስፈሪው ቦርንማውዝ

በአውሮፓ ሊግ አስደናቂ ጉዞ ላይ የሚገኘው የእንግሊዙ ክለብ ቦርንማውዝ፤ በስፔኑን ሴልታ ቪጎን 2 ለ 1 በማሸነፍ የመጀመሪያዎቹን አምስት የአውሮፓ ጨዋታዎች ያሸነፈ የመጀመሪያው የእንግሊዝ ክለብ በመሆን ታሪካዊ ክብረወሰን አስመዝግቧል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 3

በአውሮፓ ሊግ አስደናቂ ጉዞ ላይ የሚገኘው የእንግሊዙ ክለብ ቦርንማውዝ፤ በስፔኑን ሴልታ ቪጎን 2 ለ 1 በማሸነፍ የመጀመሪያዎቹን አምስት የአውሮፓ ጨዋታዎች ያሸነፈ የመጀመሪያው የእንግሊዝ ክለብ በመሆን ታሪካዊ ክብረወሰን አስመዝግቧል።

በአሰልጣኝ ማርኮ ሮሰ የሚመራው ቦርንማውዝ፣ ትናንት ምሽት በቪጎ በተደረገው የዩሮፓ ሊግ የምድብ ጨዋታ ኢያጎ አስፓስ በ19ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ቢመራም፣ ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ባፎዴ ዲያኪቴ በቀይ ካርድ ከሜዳ በመውጣቱ ከ65 ደቂቃ በላይ በ10 ተጫዋቾች ለመጫወት ተገድዷል።

ሆኖም ቦርንማውዝ በሁለተኛው አጋማሽ በአሚን አድሊ አቀባይነት አልቫሮ ሮድሪጌዝ በ47ኛው ደቂቃ የአቻነት ግብ ሲያስቆጥር፣ ተቀይሮ የገባው ራያን ደግሞ በ78ኛው ደቂቃ የማሸነፊያዋን ግብ በማስቆጠር 2 ለ 1 አሸንፏል።

በዚህም ቦርንማውዝ በታላላቅ የአውሮፓ ውድድሮች የመጀመሪያ አምስት ጨዋታዎችን ያሸነፈ ሶስተኛው ቡድን ሲሆን ከዚህ ቀደም ኑረምበርግ እና አራራት ይህንን ታሪክ ማስመዝገባቸው ይታወሳል፡፡

በዚህም ቦርንማውዝ በሁሉም ውድድሮች ተከታታይ 10ኛ ድሉን በማስመዝገብ የክለቡን ክብረወሰን አሻሽሏል። በፕሪሚየር ሊጉ አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቦርንማውዝ በአውሮፓ ሊግም የደረጃ ሰንጠረዡን እየመራ ይገኛል።

አጋራ

YouTube

አማEN