አዲሱ የማንችስተር ዩናይትድ ክፍተት…ሴኔ ላመንስ!
በማንችስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ የውድድር ዘመኑ ከምስጋና በቀር ሌላ ቅሬታ ያልተሰማበት ግብ ጠባቂው ሴኔ ላመንስ አሁን ከፍተኛ ትችት እያስተናገደ ይገኛል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1
ረቡዕ ዕለት ቀያይ ሰይጣኖቹ ስፖርቲንግ ሊዝበንን በገጠሙበት ጨዋታ ሴኔ ላመንስ ባለሜዳው ቡድን በመጀመሪያ ላስቆጠረው የፍፁም ቅጣት ምት ግብ መነሻ ሲሆን በተመሳሳይ በጨዋታው ላስቆጠሩት ሁለተኛ ግብም ትልቁን ስህተት የሰራው ራሱ ነበር።
የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ፒተር ሽማይክል ከሲቢኤስ ስፖርት ጋር በነበረው ቆይታ ማንችስተር ዩናይትድ መቼ ከቋሚ አሠላለፉ እንደሚያስወጣው አላውቅም ብሏል።
ሴኔ ላመንስ በዓለም ዋንጫው ከስፔን ጋር በተደረገው ጨዋታ ከሰራው ስህተት በኋላ በራስ መተማመኑን እንዳጣ የሚናገረው ሽማይክል እንደ ግብ ጠባቂ ጥሩ በማትሆንበት ጊዜ የተከላካዮችህን እገዛ ትፈልጋለህ እነሱ አሁን ላይ ያንን ማድረግ አለመቻላቸው ደግሞ ነገሩን ይበልጥ ከባድ ያደርገዋል ሲል ተደምጧል።
ማንችስተር ዩናይትድ ለጊዜው ላመንስን ወደ ተቀያሪ ወንበር ማውረድ የሚችል አማራጭ ያለው አይመስልም። በክረምቱ የፈረመው ካርል ዳርሎው በሶስት ዓመታት የሊድስ ቆይታው የተጫወተው 30 የሊግ ጨዋታዎች ላይ ሲሆን የ 40 ዓመቱ ቶም ሂተንም በቋሚነት ለመጫወት የሚያስችል ቁመና ላይ አይገኝም።
የማውሪሲዮ ፖቼቲኖ የረዥም ጊዜ የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ ሆኖ የሰራው ቶኒ ሄሚኔዝ ሴኔ ላመንስን ወደ ቀድሞ ብቃቱ ለመመለስ የቤት ስራ የተጣለበት ግለሰብ ይመስላል።
ፖቼቲኖ ሴኔ ላመንስን ማገዝ ነበረበት ብለው የገለፁት የተከላካይ ክፍልም ከግብ ጠባቂው ጎን ለጎን ራሱን ማሻሻል እንደሚጠበቅበት ተገልጿል።
