አረንጓዴ ሀሳቦች ወደ ተግባር:- የግሪን ፊውቸር አፍሪካ የፈጠራ ውድድር ተጠናቀቀ
በወጣቶች የሚመሩ የአየር ንብረት ፈጠራዎችንና አረንጓዴ ሥራ ፈጠራን በማበረታታት ላይ ያተኮረው የግሪን ፊውቸር አፍሪካ ሁለተኛ ምዕራፍ ተጠናቋል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 2

የመዝጊያ መርሃ ግብሩ በእንግሊዝ ኤምባሲ፣ በብሪቲሽ ካውንስል እና በጀስቲሺያ ሚዲያ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ የዲፕሎማሲ አካላት፣ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች፣ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች እና በአካባቢ ጥበቃና ዘላቂ ልማት ዘርፍ የሚሠሩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በመድረኩ በተካሄደው የፓናል ውይይት የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ፣ የወጣቶች አመራር እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ተነስተዋል።
ሥራ ፈጣሪዎቹ ያዘጋጇቸውም የአየር ንብረት ተስማሚ የንግድ ሥራዎችና የፈጠራ ውጤቶች በኤግዚቢሽን የቀረቡ ሲሆን ምህረት አማን፣ ናኦል ዳንኤል እና ማቱሳላ ሙላቸው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
ብሪቲሽ ካውንስል ከ1ኛ እስከ 10ኛ ደረጃ ለወጡት ተወዳዳሪዎች ለእያንዳንዳቸው የ200 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ያበረከት ሲሆን ከየኛ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በተደረገ ትብብር የብድር ድጋፍም ተደርጓል።
ከ1ኛ እስከ 10ኛ ደረጃ ለወጡት ከ100 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር የብድር ድጋፍ እንዲሁም ከ11ኛ እስከ 30ኛ ደረጃ ለወጡት ደግሞ የ100 ሺህ ብር ብድር ተመቻችቷል።
በመርሃ ግብሩ ወጣቶች አረንጓዴ ሥራ ፈጠራንና የተቋማትን ትብብር በማጠናከር ለአካባቢ ጥበቃና ለዘላቂ ልማት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።
#digitalhagerie #britishembassEthiopia #greenfutureafrica
