ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የፕሪሚየር ሊጉን የሀይል ሚዛን የቀየረው ዴክላን ራይስ!

አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ ዴክላን ራይስን ከዌስትሃም ለማስፈረም ያደረጉት ፉክክር የፕሪሚየር ሊጉን የሀይል ሚዛን ቀያሪ ተደርጎ ይወሰዳል።

ዜና ክፍል · · 2 ደቂቃ ንባብ · 2

በ 2023 ክረምት ዴክላን ራይስ ከዌስትሃም ጋር የአውሮፓ ኮንፍረንስ ሊግን ማሸነፍ ከቻለ በኋላ ከሁለቱ የሊጉ ሀያላን ክለቦች የዝውውር ጥያቄ ቀረበለት።

አርሰናል በዚያ ክረምት በታሪኩ አድርጎት በማያውቀው መንገድ በመጓዝ ዴክላን ራይስን ለማስፈረም ከ 100 ሚሊየን ፓውንድ በላይ አቀረበ።

ዴክላን ራይስ በወጣት አሠልጣኝ በሚመራው እና የሚያድግ ፕሮጀክት ለያዘው አርሰናል አሊያም በዓለም እግርኳስ እጅግ ስኬታማ በሆነው አሠልጣኝ ወደ ሚመራው ማንችስተር ሲቲ የማምራት ምርጫ ቀረበለት።

እንግሊዛዊው አይደክሜ አማካይ የሶስትዮሽ ዋንጫን ካሸነፉ በኋላ ገና ከድሉ ሃንጎቨር እንኳን በቅጡ ካልተላቀቁት ማንችስተር ሲቲዎች ይልቅ ስኬታማ ለመሆን ደፋቀና ወደሚሉት መድፈኞቹ ቤት ማምራትን መረጠ።

ዴክላን ራይስ ለዌስትሃም በተጫወተባቸው ስድስት ዓመታት ሁለቱ ፈላጊ ክለቦች በተመሳሳይ ደረጃ ላይ እንዳልነበሩ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር።

ማንችስተር ሲቲ በነዚህ ጊዜያት አምስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ፣ አንድ የሻምፒዮንስ ሊግ እና ስድስት ሌሎች ተጨማሪ ዋንጫዎችን ሲያሸንፍ አርሰናል ያሸነፈው አንድ የኤፍ ኤ ዋንጫ ነበር።

ራይስ አርሰናልን ከመረጠ በኋላ በመጀመሪያው ቀን ሚኬል አርቴታ በአርሰናል እየገነባ ባለው ነገር ትልቅ እምነት እንዳለው እና የሂደቱ አካል ለመሆን ዝግጁ መሆኑን ነበር የተናገረው።

አርሰናል ዴክላን ራይስን ሲያስፈርም ከቡድኑ መሪዎች አንዱ ሊያደርገው ፣ የሚወዱት እና የሚተማመኑበት ተጨዋች ሊሆን እንዲሁም የሞተሩ ወርቃማ ነዳጅ እንዲሆን እምነት ጥሎበት ነበር።

ከሶስት ዓመት ተኩል በኋላ ሁሉም ነገር በታሰበለት መንገድ ተጉዞ ሚኬል አርቴታ እና አርሰናል የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ሲያነሱ ዴክላን ራይስ ደግሞ ምርጡ ተጨዋቻቸው ነበር።

አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ በዚህ ሳምንት በኤምሬትስ ሲገናኙ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዓመታት በተቃራኒ የሀይል ሚዛኑ ለአርሰናል አድልቶ ይሆናል።

አጋራ

YouTube

አማEN