“ስፖርት ጋዜጠኝነት ጨዋታን ከመዘገብ እና ድልን ከመናገር በላይ ነው” አቶ ኢሳያስ ጅራ
አቶ ኢሳያስ ጅራ ባስተላለፉት መልዕክት የስፖርት ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ ስፖርት ውስጥ ትልቅ ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዚያ ልክ መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያደረገ ሲሆን ሲሆን በመድረኩ የተገኙት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራን ጨምሮ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አቃቢተ ነዋይ እና የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶችና ጨዋታዎች ፌደሬሽን ፕሬዝደንት ወ/ሮ ህይወት መሀመድ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አሰግደው ወ/ጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት ኮማንደር ስለሺ ስህን እና የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት ፍትህ ወ/ሰንበት (ዶ/ር) በጉባኤው ተገኝተዋል።
አቶ ኢሳያስ ጅራ ባስተላለፉት መልዕክት የስፖርት ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ ስፖርት ውስጥ ትልቅ ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዚያ ልክ መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው ስፖርት ጋዜጠኝነት ጨዋታን ከመዘገብ እና ድልን ከመናገር ያለፈ ነው ብለዋል።
ስፖርት በባህሪው ብዙ ውጣ ውረድ ያለው ቢሆንም ሀገራዊ ኩራት መሆኑ መዘንጋት የለበትም ያሉት ፕሬዝደንቱ የስፖርት ሚዲያው በዋናነት የስፖርት ተቋማት ተጠያቂነት እንዲኖራቸው በመስራት ከፍ ብሎ መገኝት እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።
አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበርን የማገዝ ሃላፊነት እንዳለባቸው እና ማህበሩ በሙሉ አቅሙ እንዲሰራ ማድረግ የሁሉ ፌደሬሽኖች ሃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።
