ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

“በአምስት ዓመታት ውስጥ ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ ለሕዝባችን ቃል ገብተናል” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በአምስት ዓመታት ውስጥ መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ለሕዝብ ለማስረከብ የተገባውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ ቀን ከሌት ያለ እረፍት እየተሠራ መሆኑን አስታወቁ።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ሕዝቡ በመኖሪያ ቤት እጥረት ምክንያት የሚገጥመውን ፈተናና ስጋት በሚገባ እንደሚረዱ ገልጸዋል።

ደረጃቸውን የጠበቁና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ መኖሪያ ቤቶችን ማመቻቸት የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን የዜጎች አደራና ኃላፊነት መሆኑን ጠንቅቀው እንደሚገነዘቡም አመልክተዋል።

አያይዘውም ዋነኛ ትኩረታቸው ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ የሕዝቡን የመኖሪያ ቤት ጫና ማቃለል እና በመላው አገሪቱ ለሚገኙ ቤተሰቦች የተሻለ የኑሮ ምዕራፍ መክፈት መሆኑን አስገንዝበዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN