የኮፕ 32 አንዱ ትኩረት የሆነው ቡና በአንታሊያ እየተዋወቀ ነው
ኢትዮጵያ በቀጣይ በምታዘጋጀው የኮፕ 32 (COP 32) ዓለም አቀፍ ጉባኤ ትኩረት ከተሰጣቸው አበይት ጉዳዮች መካከል አንዱ ቡና መሆኑ ተገለጸ።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

በተርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 31) ጎን ለጎን ኢትዮጵያን የማስተዋወቅ ሥራ በስፋት እየተሠራ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናግረዋል።
በዚሁ መድረክ የጉባኤው ተሳታፊዎች በፓቪሊዮኑ እየተገኙ የኢትዮጵያን ቡና እንዲቀምሱና እንዲያውቁት በማድረግ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እየተዋወቀ መሆኑ ተመላክቷል።
ኢትዮጵያ የቡና መገኛ እንደመሆኗ መጠን ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ ከሆኑ ምርቶች ቀዳሚው ቡና መሆኑን ኃላፊዋ ገልጸዋል። አያይዘውም ቡና ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን በየዕለቱ የዓለምን ሕዝብ የሚያነቃቃ በመሆኑ ሁሉም አካል ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል።
