ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ቼልሲ ጥሩ ቁጥሮችን በያዘበት ሜዳ ይጫወታል!

12ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ጅማሮውን ሲያደርግ ቼልሲ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ኖቲንግሃም ፎረስትን ምሽት 5:00 ሰዓት ይገጥማል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ስምንተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ በመጨረሻዎቹ ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች በሰንደርላንድ እና በሊድስ ዩናይትድ ከደረሰበት ሽንፈት ለማገገም እንደሚጫወት ይጠበቃል።

ምንም እንኳን ሰማያዊዎቹ አሁን ላይ በወጥነት ምርጥ ብቃት እያሳዩ ባይገኙም የክለቡ አመራሮች የአሠልጣኝ ለውጥ ከማድረግ ይልቅ በትዕግስት የነገሮችን ሂደት መመልከት እንደሚመርጡ ተሰምቷል።

ለስፔናዊው አሠልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ከሳምንት በፊት በስታምፎርድ ብሪጅ በሊድስ የደረሰበት ሽንፈት የባየር ሌቨርኩዘን አሠልጣኝ በነበረበት ወቅት በፖርቶ 3 ለ 0 ከተሸነፈ በኋላ በሜዳው የደረሰበት ትልቁ ሽንፈት ሆኖ ተመዝግቧል።

ተጨዋቾቹ በዛሬው ጨዋታ ጠንካራ ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው የገለፀው አሎንሶ ትናንት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሞይሰስ ካይሴዶ ለጨዋታ ዝግጁ መሆኑን ግን ደግሞ አሁንም ቡድኑ ያለ ብራዚላዊው ጆኣኦ ፔድሮ ጨዋታውን እንደሚያደርግ ይፋ አድርጓል።

በኦሊቨር ግላስነር የሚመሩት ኖቲንግሃም ፎረስቶች ባሳለፍነው ሳምንት በቦርንመዝ የደረሰባቸው ሽንፈት በደረጃ ሰንጠረዡ 17ኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጡ አስገድዷቸዋል።

ኦስትሪያዊው አሠልጣኝ በፕሪሚየር ሊጉ 100ኛውን ጨዋታቸውን በሽንፈት ቢደመድሙም በሜዳቸው በሚያደርጉት ጨዋታ ቼልሲን በአሠልጣኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ግምት አግኝተዋል።

ቼልሲ ምንም እንኳን ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ያደረገውን ጨዋታ በሽንፈት ቢያጠናቅቅም በሲቲ ግራውንድ ጥሩ ታሪክ አለው።

ሰማያዊዎቹ ወደ ሲቲ ግራውንድ አምርተው ባደረጓቸው የመጨረሻ አምስት ጨዋታዎች ምንም አይነት ሽንፈት አልተመለከቱም ከነዚህ ውስጥ አራቱን በድል አጠናቀዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN