ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

አሜሪካ በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍና የኢኮኖሚ መነቃቃትን ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋገጠች

የአሜሪካ ኤምባሲ የወጣው መልዕክት እንደሚያመለክተው፣ አምባሳደር ማሲንጋ ከሌሎች አምባሳደሮች ጋር በመሆን ወደ መቐለ ባደረጉት የጋራ ጉዞ አሜሪካ በትግራይ ክልል በኢኮኖሚ የዳበረና ዴሞክራሲያዊ መጻኢ ዕድል እንዲኖር ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

አምባሳደሩ ከአካባቢው አመራሮችና ከሲቪል ማኅበረሰብ አካላት ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች መረጋጋት፣ አካታችነት እና ጠንካራ ተቋማት ለሁሉም የትግራይ ነዋሪዎች የኢኮኖሚ እድገትና የዕድል መፈጠር ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይሎች መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በተጨማሪም አምባሳደር ማሲንጋ በቀጠለው ድርቅ ለተጎዱ ማኅበረሰቦች ሕይወት አድን የሆነ ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እንዲሆን አሜሪካ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

አያይዘውም ትግራይና መላው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢ ወደፊት መጓዝ እንዲጀምሩ ለመደገፍ ሀገራቸው ከክልሉ ሕዝብ፣ ከፌዴራል መንግሥት እንዲሁም ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በትብብር እንደምትሠራ አስታውቀዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN