የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት አዳዲስ አመራሮች
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዳዲስ አመራሮችን ያካተተ ምርጫ በማካሄድ የአባላቱን ብዛት ከአምስት ወደ ሰባት ከፍ አድርጓል
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

ምክር ቤቱ የኃላፊነት ድልድልም ተሰጥቷል፦
👉አቶ አማረ አረጋዊ (የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት) – የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
👉አቶ ብሩክ ከበደ (የኤንቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ) – ምክትል ሰብሳቢ
በዘርፍ አመራርነት:
👉አቶ ነብዩ ጥዑመልሳን – የኢቢኤስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
👉አቶ መሰረት አታላይ – የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት
👉ወ/ሮ ፍሬዘር ነጋሽ – የኢትዮጵያ የበይነመረብ ሚዲያ ማኅበር ፕሬዚዳንት
👉አቶ ጥበቡ በለጠ – የአሐዱ ሬዲዮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
አዲሱ አመራር በቀጣዮቹ ዓመታት ምክር ቤቱን በተጠናከረ እና በአዲስ መልክ ወደ ሥራ እንደሚያስገባ ገልጿል። በተጨማሪም የሚዲያ ማኅበረሰቡ፣ የመንግሥት ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለተቋሙ ስኬት በትብብር እንዲሠሩ ጥሪውን አቅርቧል።
በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀጽ 57(1) መሠረት በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የተመዘገበው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት፤ ከ100 በላይ የሕዝብ፣ የንግድ፣ የማኅበረሰብ እና የበይነመረብ ሚዲያዎችን እንዲሁም የጋዜጠኞች ሙያ ማኅበራትን በአባልነት በማቀፍ የሚዲያውን የራስ ቁጥጥር ሥርዓት እያስፈጸመ እንደሚገኝ በመግለጫው አስታውቋል።
