ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

“የአየር ንብረት ፈንዶች ተደራሽነትና ውጤታማነት ሊያድግ ይገባል” – ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር)

ከዓለም አቀፉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP31) ጎን ለጎን በተዘጋጀ መድረክ ላይ የባለብዙ ወገን የአየር ንብረት ፈንዶች ተደራሽነት እንዲሰፋና ውጤታማነታቸው እንዲያድግ ጥሪ ቀረበ።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 3

ከዓለም አቀፉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP31) ጎን ለጎን በተዘጋጀ መድረክ ላይ የባለብዙ ወገን የአየር ንብረት ፈንዶች ተደራሽነት እንዲሰፋና ውጤታማነታቸው እንዲያድግ ጥሪ ቀረበ።
ጥሪውን ያቀረቡት በጉባኤው ጎን ለጎን “ባለብዙ ወገን የአየር ንብረት ፈንዶች፡ ለተሻለ ተደራሽነትና ለላቀ ተጽዕኖ በጋራ መሥራት” በሚል ርዕስ በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትሯና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ናቸው።
ዶ/ር ፍጹም በንግግራቸው ታዳጊ ሀገራት ያስቀመጧቸውን የአየር ንብረት ቅድሚያ ተግባራት በተሟላ መልኩ ማሳካት እንዲችሉ የባለብዙ ወገን የአየር ንብረት ፈንዶች ጉልህ ሚና እንዳላቸው ጠቁመዋል።
ለዚህም ይረዳ ዘንድ ዓለም አቀፍ ትብብርን ይበልጥ ማጠናከር፣ የፋይናንስ አቅርቦት ተደራሽነትን ማስፋት፣ እንዲሁም ፈንዶቹ በተጨባጭ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆነው እንዲሰሩ ውጤታማነታቸውን ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው አስረድተዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN