ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ በአየር ንብረት ፋይናንስና በCOP32 ዝግጅት ዙሪያ ተወያዩ
በተርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ከሚገኘው የCOP31 የአየር ንብረት ጉባኤ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከዓለም ባንክ ቡድን ዋና ዳይሬክተር እና ቺፍ ኖውሌጅ ኦፊሰር ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 2

ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው ለቀጣዩ COP32 ዝግጅት የሚደረገውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የመከሩ ሲሆን፤ በአየር ንብረት ፋይናንስ፣ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ አፈጻጸም እንዲሁም በካርቦን ክሬዲት ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ምክክር አድርገዋል።
