ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከባርቤዶስ አቻቸው ሚያ ሞትሊ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ጋር በሁለትዮሽ እና የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 2

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ጋር በሁለትዮሽ እና የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ እንዳስታወቁት የምክክሩ ዋና ትኩረት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የአቪዬሽን ትብብር ማጠናከር እንዲሁም የኢትዮጵያን የCOP32 ፕሬዝዳንትነት ለመደገፍ በሚደረገው አጋርነት ላይ ያተኮረ ነበር።
በተጨማሪም ውይይቱ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ፍላጎቶች መሠረት በማድረግ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ይበልጥ ለማስፋት ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።
የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የወል ጉዳዮች ላይ በቅንጅት በመስራት፣ ውይይቱን ወደ ተጨባጭ ውጤቶች ለመቀየር የሚያስችል ገንቢ ምክክር መደረጉንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN