ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

በምክክር የጸናችና ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ይገባል – አፈጉባኤ ሙፈሪያት ካሚል

የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሀገራዊ የምክክር መድረኩ ማጠቃለያ በስኬት ተካሂዶ ለቀጣዩ ምዕራፍ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት መከበሩ ለዲሞክራሲያዊ ባህል ግንባታ ትልቅ መደላድል እንደሚፈጥር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ሁለንተናዊ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠች፣ አምራች፣ መሪና ስልጡን ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የትውልድ ፍኖት ተቀርጾ በርካታ የሥልጠና ሥራዎች ሲካሄዱ መቆየታቸው ተመላክቷል።

የተያዘው በጀት ዓመት ሕዝቡ ይሆነኛል ያለውን አካል በዲሞክራሲያዊ መብቱ መርጦ መንግሥት የመሠረተበት መሆኑንና ልዩነቶችን በኃይል ሳይሆን በሰለጠነ አግባብ የመፍታት ባህል መዳበሩን የገለጸው መግለጫው የተግባባ ሕዝብ ያለው ሀገር የተፋጠነ እድገት እንደሚኖረው አጽንኦት ሰጥቷል።

በመጨረሻም መላው ኢትዮጵያውያን ጠንካራ አንድነቷን ያረጋገጠች ሁለንተናዊ ሉዓላዊነቷን እውን ያደረገች መሪ አምራች የሆነች ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ረገድ እጅ ለእጅ ተያይዘን ኃላፊነታችንን እንድንወጣ በማለት ጥሪ ቀርቧል።

አጋራ

YouTube

አማEN