“የሱዳን ጦርነት ወጣቶችን ለከፋ የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት ዳርጓል”
ከሚያዚያ 2023 ጀምሮ በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ያስከተለው የስነ-ልቦና ቀውስና መፈናቀል ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ወጣቶችን ለአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት እየዳረጋቸው መሆኑን አልጀዚራ ዘገበ።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ቢያንስ 59 ሺህ ሰዎችን ለሞት የዳረገውና 14 ሚሊዮን ዜጎችን ያፈናቀለው ግጭት ህክምና ፈላጊዎችን አብዝቷል።
በካርቱም የሚገኘው የቃድሪን የሱስ ህክምና ማዕከል ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በስነ-ልቦናና በሱስ ችግር የተጎዱ 10 ሺህ 1 መቶ ታካሚዎችን መቀበሉን ሲገልጽ ባለሙያዎች ዕፁ በቀድሞ የRSF ይዞታዎች ወጣቶችን ለውጊያ ለመመልመል ጥቅም ላይ መዋሉን ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል የሱዳን ጸረ-አደንዛዥ ዕፅ መምሪያ ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ አል-ሙአተሲም ኦካሻ ጦሩ ከካርቱም በስተሰሜን ቀደም ሲል በRSF ስር በነበረ አካባቢ በሰዓት 100 ሺህ የካፕታጎን ክኒኖችን ማምረት የሚችል የ3 ሚሊዮን ዶላር ፋብሪካ መገኘቱንና የአደንዛዥ ዕፅ ምርትና ዝውውር የጦርነት መሳሪያ መሆኑን ገልጸዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
