ኒኮ ፓዝ የብሩኖ ፈርናንዴዝ ተተኪ?
ማንቸስተር ዩናይትድ ብሩኖ ፈርናንዴዝን ለመተካት አርጀንቲናዊውን የኮሞ አማካይ ኒኮ ፓዝን በዝውውር ዝርዝሩ ውስጥ አካተተ።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1
ኮሞ በ2024 ፓዝን ከሪያል ማድሪድ በ6 ሚሊዮን ዩሮ ሲያስፈርም ማድሪድ በቀጣዮቹ ሦስት የክረምት የዝውውር መስኮቶች ተጫዋቹን በቅደም ተከተል በ8 ፣ በ9 እና በ10 ሚሊዮን ዩሮ መልሶ የመግዛት ውል አስቀምጦ ነበር።
ሆኖም ባለፈው ሰኔ ወር ውሉ ተሻሽሎ ኮሞ ለማድሪድ 60 ሚሊዮን ዩሮ እንዲከፍልና የሪያል ማድሪድ መልሶ የመግዛት መብትም በ2027 ብቻ ተግባራዊ የሚሆን የ80 ሚሊዮን ዩሮ ውል እንዲሆን ተደርጓል።
በአሀኑ ሰዓት የተጨዋቹ ፈላጊዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን ለአብነትም ማንቸስተር ዩናይትድ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ኦልድትራፎርድን የሚለቅ ከሆነ እሱን ለመተካት ካሰባቸው ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ ኒኮ ፓዝን አካቷል።
የ2026-27 የውድድር ዘመን ሲጠናቀቅ ኮንትራቱ የሚያበቃው ፈርናንዴዝ ውሉን ለማራዘም ሲደረግ የነበረው ድርድር መቆሙን በቅርቡ አረጋግጧል።
ዘ አትሌቲክ ባወጣው ዘገባ ምንም እንኳን አሁን ላይ ማንቸስተር ዩናይትድ የኒኮ ፓዝ የመጀመሪያ ምርጫ ባይሆንም የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ፣ የዩናይትድ የወደፊት ፕሮጀክት እና ክለቡ አስቀድሞ የገነባው ታላቅ ስም ተጨዋቹን ሊስቡ እንደሚችሉ ጠቁሟል።
በተጨማሪም የሀገሩ ሰው ከሆነው አሰልጣኙ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ጋር አንድ ዓይነት ወኪሎች መጋራቱ ለዝውውሩ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።
ይህም ሆኖ የ22 ዓመቱን ወጣት ተጫዋች ለማስፈረም የሚደረገው ፉክክር እጅግ ብርቱ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን ማንቸስተር ዩናይትድም ለዚህ ቦታ ሌሎች አማራጮችን እየተመለከተ ይገኛል።
