ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር እና ዋናው ስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት የአጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ

ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ በጋራ ለመስራት የተስማሙ ሲሆን በዋናነት የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር በቀጣይ ለሚሰራቸው ትልልቅ ስራዎች ዋናው ስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት በአጋርነት እንደሚሰራ የማህበሩ ፕሬዝደንት ንዋይ ይመር ተናግረዋል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 5

ስምምነቱ ማህበሩ የሚያደርጋቸውን ጠቅላላ ጉባኤዎች ጨምሮ ሌሎች ስራዎች ለመስራት ዋናው ትጥቅ አምራች ድርጅት ለማህበሩ እገዛ የሚያደርግበት መሆኑን ፕሬዝደንቱ ተናግረዋል።

የዋናው ትጥቅ አምራች ድርጅት ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀብተስላሴ ገ/ክርስቶስ ከኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ጋር በመስራታችን ደስተኞች ነን ያሉ ሲሆን የመጣነው የስፖርት ሚዲያው ለሀገር የሚያበረክተውን መልካም ነገር ሁሉ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው ብለዋል።

ስራ አስኪያጁ ስፖርቱን እንድናውቅና እንድንወድ ያደረጋችሁን እናንተ የስፖርት ጋዜጠኞች ናችሁ በዚህም ከማህበሩ ጋር በመስራታችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል።

በቀጣይ የማህበሩን አቅም ለማሳደግና ስፖርቱን ወደ ተሻለ ከፍታ ለማድረስ አብረው እንደሚሰሩ አቶ ሀብተስላሴ ገ/ክርስቶስ ተናግረዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN