ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የኢትዮጵያ ንጹሕ ኃይል ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኢንቨስትመንት ምቹ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ከታዳሽ ምንጮች የሚመነጭ መሆኑ በኃይልና በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ማምረቻ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ምቹ ዕድል መፍጠሩን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር መልዕክት ሳህሉ ከቻይና የሲቹዋን ግዛት የንግድ ልዑካን ቡድን መሪ ሚስተር ሊያንግ ዮንግ ጋር በነበራቸው ውይይት፤ የግዛቱ ባለሀብቶች በታዳሽ ኃይል፣ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በማዕድን ዘርፎች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ያላቸው ፍላጎት ከሀገሪቱ የልማት ግብ ጋር የተጣጣመ መሆኑን አስረድተዋል።

የሲቹዋን ግዛት ተወካይ ሊያንግ ዮንግ በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለው የኢንዱስትሪ ዕድገት አበረታች መሆኑን ጠቅሰው በርካታ ኩባንያዎችን ወደ ሀገሪቱ በማምጣት በዘርፎቹ ለማሰማራት ከኮሚሽኑ ጋር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN