ሀገሬ ቲቪ

ትምህርት ዘግታ የከረመችው ኡጋንዳ

ለሁለት ዓመት ትምህርት ቤቶቿን የዘጋችው ኡጋንዳ እንደገና መክፈቷን አስታወቀች፡፡ ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ በኡጋንዳ ከ15 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ድርሽ ብለው እንደማያውቁ ነው የተነገረው፡፡ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ደግሞ ምክንያት ሆኖ ተቀመጧል፡፡ ኡጋንዳ በዚህ ድርጊቷ ለረጅም ጊዜ ትምህርት ቤቶችን በመዝጋት የዓለማችን ቀዳሚዋ ሀገር ሆናለች፡፡ ትምህርት መከፈቱን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ካምፓላ ከወተወሮ የተለየ የመንገድ መጨናነቅ ታይቷል፡፡ አሁን ላይ ታዲያ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው በመመለስ ያቋረጡትን ትምህርት እንደሚቀጥሉ የሀገሪቱ ትምህርት ሚንስቴር አስታውቋል፡፡ የመማር ማስተማር ሥራውን ቀና ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት መከናወኑም ነው ሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ ለኤፍፒ ኒውስ የተናገረው፡፡ ከቅድመ ወረርሽኙ በፊት ሲያስከፍሉ ከነበረው ክፍያ በላይ የሚጠይቁ የግል ትምህርት ተቋማት ቅጣት ስለሚጣልባቸው ከእንደዚህ ዓይነት ተግባር እንዲታቀቡ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡ ኡጋንዳ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ትምህርት ቤቶችን መዝጋቷ በተለያዩ የህጻናት መብት ተሟጋቾች ሲያስኮንናት አንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2022-01-11