የጋና ባለስልጣናት ኢኮኖሚውን በአግባቡ እየመሩ አይደለም በሚል በሀገሪቱ መዲና አክራ ለተቃውሞ ወደ አደባባይ የወጡ ሰዎችን ፖሊስ አስሯል ሲል አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል።
ሰልፈኞቹ፤ በጋና ማዕድን የሚወጣበት መንገድ አካባቢን የሚበክል ነው ይህም የሀገሪቱ ባለስልጣናት ዘርፉን በአግባቡ እየመሩ አለመሆናቸውን የሚያሳይ ነው ማለታቸውንም ዘገባው ጠቁሟል።
የጋና ፖሊስ ሰልፈኞቹ የፖሊስ መኮንኖች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በሚል ወንጅሎ ማሰሩ የተገለጸ ሲሆን፤ ‘’ዲሞክራሲ ሀብ’’ የተሰኘው ሰልፍ አስተባባሪ ተቋም በበኩሉ፤ ፖሊስ ንጹሃን ሰዎችን ሲደበድብ እንደነበር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ይህ የዜጎች ተቅቃውሞ የመጣው ጋና በወርሃ ህዳር ላይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማከናወን በዝግጅት ላይ ባለችበት ወቅት ነው ተብሏል።
በበላይሁን ፍሰሃ
2024-09-24