የሶማሊያ ደኅንነት ባልተረጋጋበት በዚህ ወቅት፤ በውጭ ሀገራት ለሶማሊያ የሚደረገው የጦር መሳሪያ ድጋፍ በአሸባሪዎች እጅ ላይ እንዲውድቅ ያደርገዋል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ተናገሩ።
አምባሳደሩ ይህን የተናገሩት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ግንባታ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሐፊ ሮዝማሪ ዲካርሎ ጋር በአሜሪካ በመከሩበት ወቅት ነው ተብሏል።
አምባሳደሩ አክለው፤ የፊታችን ታህሳስ ወር ላይ ተልዕኮው በሚጠናቀቀው ሰላም አስከባሪ ጦር ምትክ በሚገባው ኃይልን በተመለከተ ጊዜ ተወስዶ መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል።
ግብጽ ወደ ሶማሊያ የጦር መሳሪያዎችን እየላከች ስለመሆኑ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።
በበላይሁን ፍሰሃ
2024-09-24