ሀገሬ ቲቪ

በቡርኪና ፋሶ ታጣቂዎች ጉዳት አደረሱ።

ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው የቡርኪና ፋሶ ታጥቂ ቡድኖች ባደረጉት ተኩስ 12 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።

ከ2015 ጀምሮ በሀገሪቱ ትጥቅ አንግቦ የሚንቀሳቀሰው ቡድን እስካሁን ድረስ በ10 ሺ የሚቆጠሩትን ለሞት ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን የሀገሪቱን ዜጎች ለመፈናቀል ዳርጓቸዋል።

በታጣቂዎቹ በኩል የተባለ ባይኖርም በአካባቢው ያሉ እማኞች እንደሚሉት ቡድኑ ንፁሃንን የገደላቸው ከሀገሪቱ መንግሥት ወታደሮች ጋር ትብብር ስለሚያደርጉ ነው ተብሏል።

እ.አ.አ በ2022 በመፈንቅለ መንግሥት ስልጣን የያዘው የሀገሪቱ ወታደር ዋና ዓላማው ሀገሪቱን ከሽብር እንዲሁም እስላማዊ ታጣቂ ብድኑ ከሚያደርጋቸው ግድያዎች ንፁኃንን መታደግ መሆኑን መናገሩ አይዘነጋም።

በአስናቀ ማናዬ
2024-08-26