የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕወሃት በደቡብ አፍሪካ በጀመሩት ንግግር ከወዲሁ ለሰላም ያሳዩት ቁርጠኝነትና ለግጭቱ ዘላቂ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማስገኘት ያላቸው ቀናዒነት አበረታች ነው አሉ።
የሰላም ንግግግሩን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ፣ የኬንያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ፉምዚል ማላምቦ ናጉዋ እየመሩት እንደሆነም ገልጸዋል።
አሜሪካ፣ ተመድና ኢጋድ በታዛቢነት እየተሳተፉ መሆኑን ፋኪ አስታውቀዋል። የሰላም ንግግሩ እስከ መጭው እሁድ እንደሚቀጥል የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
በብሩክ ያሬድ
2022-10-26
