በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ውስጥ በዚህ ክረምት ብቻ ከባድ ዝናብን ተከትሎ በተከሰተ ጎርፍ ምክንያት እስከአሁን 25 ሰዎች መሞታቸዉ ተገለጸ።
በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ዉስጥ ከወርሃ ሰኔ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 22 ቀን ድረስ በደረሱ አደጋዎች፤ 25 ሰዎች እና 170 እንስሳት ሲሞቱ፤ 1 ሺሕ 713 ሄክታር በዘር የተሸፈነ መሬት ጉዳት እንደደረሰበት ዞኑ ማስታወቁን ትግራ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
በጎርፉ ምክንያት 297 መኖሪያ ቤቶች መፍረሳቸውንም ዘገባው ጠቁሟል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ትንበያ መሰረት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ መጣሉን ሊቀጥል ስለሚችል ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም ዞኑ አሳስቧል።
በበላይሁን ፍሰሃ
2024-08-29