በሻይ ቅጠል ልማት ላይ ባለሀብቶች በስፋት እየተሳተፉ ባለመሆናቸው ሀገሪቱ ማግኘት ያለበትን የውጪ ምንዛሪ እንዳታገኝ እንቅፋት እየሆነባት መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ2 ሚሊዮን በላይ ዶላር ገቢ መገኘቱ የተነገረ ሲሆን ይህም ከ2015 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ0. 33 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ያለው ነው ተብሏል።
በበጀት ዓመቱ የተላከው የሻይ ቅጠል ምርት ለውጭ ገበያ የተላከው ከ2015 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር የ50 ሺህ ቶን ብልጫ ቢኖረውም ሀገሪቱ ካላት አቅም አንጻር ብዙ መሥራት የሚጠይቅ መሆኑ ተነግሯል።
የሻይ ቅጠል ምርትን ለማስፋት ከአርሶ አደሮች በተጨማሪ ባለሀብቶች በስፋት ሊሳተፉ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
በብሩክታዊት አሥራት
2024-09-24