በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እራሳቸውን ከሽብር ጥቃት እንዲጠብቁ በሊባኖስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት አስታወቀ።
በሊባኖስ እና በቀጣናው ያለው ውጥረት ተባብሶ መቀጠሉን ፅ/ቤቱ ገልጿል።
በተለይም በደቡባዊ ሊባኖስ እንዲሁም በቤሩት አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል ብሏል።
የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ሁኔታውን እየተከታተለ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የጥቃት ኢላማ ተብለው ከተለዩ ወይም ከሚታሰቡ አካባቢዎች እራሳቸውን እንዲያር አሳስቧል፡፡
ከሊባኖስ መንግስት የሚሰጡ መመሪያዎችን እና አቅጣጫቸውን መተግበር እንደሚገባ ያነሳው ጽ/ቤቱ፣ ያለው ሁኔታ እየከፋ የሚሔድ ከሆነ በቀጣይ የሚወሰዱ እርምጃዎች ይፋ ስለሚደረጉ በቆንስላውን ማህበራዊ ትስስር ገፅ የሚለቀቁ መረጃዎችን መከታተል እንደሚገባቸው አሳስቧል።
በተጨማሪም የከፋ ሁኔታ በሚገጥማችሁ ወቅት በቆንስላው ቀጥታ ስልክ መስመር እንዲያሳውቁም ጠይቋል።
በማህሌት አማረ
2024-09-24