ሀገሬ ቲቪ

ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመሸጥ የመሰረተ ልማት ግንባታው እየተፋጠነ ነው

ኢትዮጵያ ለኬንያ ለምትሽጠው የኤሌክትሪክ ሃይል የሚሆነው የመሠረተ ልማት ግንባታ እየተፋጠነ እንደሚገኝ መመልከታቸውን በኬኒያ ኢነርጂና ነዳጅ ሚኒስቴር የካቢኔ ጸሐፊ ሞኒካ ጁማ ገለጹ።

ሞኒካ ጁማ በኬኒያ በኩል የሚገኘው 612 ኪሎ ሜትር የመሰረተ ልማት ግንባታንም በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያና ኬኒያ ባሳለፍነው ሐምሌ ወር 200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል።

ስምምነቱ ኢትዮጵያ አሁን ላይ 200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለኬንያ ለመሸጥ የሚያስችላት ሲሆን በቀጣይሞ የአቅርቦቱን መጠን እስከ 400 ሜጋ ዋት ከፍ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

በብሩክ ያሬድ
2022-10-26