ሀገሬ ቲቪ

በሱዳን ተቃውሞ እየተካሄደ ነው

በሱዳን ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ያስቆመውን መፈንቅለ መንግስት አንደኛ አመት በማስመልከት በመላ ሀገሪቱ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው ።

በሰልፉ የሀገሪቱ የጦር ኃይል አዛዥ አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን በሀገሪቱ ምንም አይነት ለውጥ አላመጡም የሚሉ መፈክሮች ተስተውለዋል።

የሱዳን ወታደራዊ ገዥዎች ለዴሞክራሲያዊ ማሻሻያ ያላቸውን ቁርጠኝነት ቢገልጹም በ2019 ኦማር አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ቃል የገቡትን በማጠፍ የስልጣን ዘመናቸውን በማራዘም ላይ ይገኛሉ።

በመሆኑም ወታደራዊ መንግስቱ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በሚቀሰቀሱ አምጾች እስካሁን ከ አንድ መቶ በላይ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ተሰደዋል ተብሏል ።

በብሩክ ያሬድ
2022-10-26