ሀገሬ ቲቪ

ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞች የቴሌ ክላውድ አገልግሎትን በይፋ አስጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም ድህንነቱ የተጠበቀ የቴሌ ክላወድ አገልገሎት ዛሬ በይፋ አስጀምሯል ።አገልገሎቱ ተቋማት የመረጃ ማዕከል መገንባት ሳይጠበቅባቸው በፈለጉበት ቦታ ሆነው መረጃን ማስቀመጥ ፣መቀመር የሚችሉበትም ነው ተብሏል።

አገልገሎቱን ያስጀመሩት የአቲዮ ቴለኮም ዋና ሰራ አጸፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ አሁን የጅመረው የክለወድ ሲሰተም ብዙ ጉልበት የሚቀንስ እና ወጪን የሚቆጥብ ነው በልዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የሦስት አመት አዲስ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ መሥራት ከጀመረ ሦስት ወራት መቆጠራቸውን ገልጸው፤ የክላውድ አገልግሎቱም የዚሁ ዕቅድ አካል ነው ብለዋል።

አገልገሎቱ በሃገራችን ከግዜ ወድ ግዜ እየጨመረ የመጣወን የግል እና የመንግስት የመረጃ ክምችትን ለማስለጥ ያግዛል ተበሏል ።

ይፋ የሆነው የክላውድ አገልግሎት በማኑዋል ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶችን በሲስተም እንዲታገዙ በማድረግ የቢዝነስ ስራን ቀላል ምቹና አስተማማኝ በማድረግ ውጤታማ እንዲሆኑ ያስችለዋል ተብሏል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-10-27