ሀገሬ ቲቪ

ኢትዮጵያ ብቁ የሆነ የሰው ሀብት እንዲኖራት የሚሰራ ማህበር ተቋቋመ

በሀግራችን የሰው ሀብት ለማፍራት የሚሰሩ የተለያዩ ተግባራት ቢኖሩም ሀገሪቱ አሁን ባለችበት የዕድገት ጎዳና ግን በቂ ነው ተብሎ አይታሰብም ።

ሀገሪቱ ከፍተኛ የወጣት ቁጥር ያላት ሲሆን ያለውን እምቅ አቅም አውጥቶ ጥቅም ላይ የማዋል ስራ ብዙ አልተሰራም ።

ታዲያ የሰው ሀብት ለማፍራት የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ እንዲሁም ሀገሪቱን በክህሎት ልማት ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ ለማድረግ ያሰበ አሶሴሽን ታለንት ዲቨሎፕመንት ኢትዮጵያ የሚባል ማህበር ተመስርቷል ።

ሀገር ወደፊት እንድትሻገር ከምንም በፊት ብቁ የሆነ የሰው ሀብት ማልማት ያስፈልጋል ያሉን የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ይህ ማዕከልም ይሄን ታሳቢ በማድረግ እንደተመሰረተ ይናገራሉ ።

ማህበሩ 5000 የሚጠጉ የዘርፉ ፕሮፌሽናሎችንና ተቋማትን በአባልነት አቅፎ ለመንቀሳቀስ አቅዷል ብለዋል።

ይህ ለትርፍ ያልተቋቋመው ማህበር ጠንክሮ ግቦቹን እንዲያሳካ ግለሰቦች እንዲሁም ተቋማት በአባልነት በመቀላቀል ከሀገር አልፎ ለሌሎች የሚተርፍ የሰው ሀብት በማፍርት አስተዋጾ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-10-27