ሀገሬ ቲቪ

ተቋርጦ የነበረውን ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የማስመለስ ስራ ሊጀመር ነው

ተቋርጦ የነበረውን ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የማስመለስ ስራ ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የማስመለስ ስራንውን የሚመራው ብሔራዊ ኮሚቴ ተመላሾች የሚያርፉባቸውን መጠለያ ቦታዎች ጎብኝቷል ።

ጉብኝቱ በየመጠለያዎቹ ለተመላሾች መሠረታዊ አገልግሎት የሚሆኑ የግብዓት አቅርቦት መሟላቱን ለማየትና፣ ሥልጠና ሰጥቶ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ለማደረግ ምን ያህል ምቹ ነው የሚለውን ለመገምገም ታስቦ የተዘጋጀ ነው ፡፡

እስከ አሁን በሳዑዲ አረቢያ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ከ71 ሺህ በላይ ዜጎችን ወደ አገር ቤት መመለስ እንደተቻለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በብሩክ ያሬድ
2022-10-27