በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በጸጥታ ችግር ከ69 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል፡፡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መፍትሄ የታጣለት በጸጥታ ችግር ሳብያ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል ብሏል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም መንገሻ ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ያልተመለሱት ታጣቂዎች ከ100 በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶችን በማውደማቸው ነው" ብለዋል፡፡ ተማሪዎቹን ወደ ትሞህርት ገበታቸው ለመመለስ የክልሉ መንግሥት ጥረት እያደረገ ቢሆንም፤ የሚመለሱበት ጊዜን ለመወሰን ግን አዳጋች መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በ2014 ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ ከነበረባቸው 300 ሺሕ ተማሪዎች መካከል 100 ሺሕ የሚጠጉት አልተመለሱም፡ ለ70 ሺሕ የተጠጉ ተማሪዎች ደግሞ ያልተመለሱት በጸጥታ ችግር መሆኑን የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዬ ዘግቧል፡ በክልሉ በመተከል እና ካማሽ ዞን ያለው የታጣቂዎች ጥቃት ክንዱን በማበርታት ተማሪዎችን ለፍርሃት ዳርጓል፡፡ ባለፉት 3 ዓመታት በክልሉ በተፈጠረው ግጭት በርካቶች ህይወታቸው ሲያልፍ በመቶሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለመፈናቀል ተገደዋል፡፡
በሀገሬ ቲቪ
2022-01-12
