ሀገሬ ቲቪ

አኮቦ ሚንራል ኩባንያ በድቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ወርቅ ለማውጣት ቁፋሮ ጀመረ

አኮቦ ሚንራል የተሰኘው በድቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በወርቅ ማውጣት ስራ ላይ ለመሰማራት ፍቃድ የወሰደ ኩባንያ የቁፋሮ ስራ መጀመሩን አስታወቀ ።

የአኮቦ ሚንራል ዋን ስራ አስፈጻሚ ጆርገን ቨጀን ይህ ለኩባን ያው የወደፊ እቅድ ስኬት መሰረት የጣለ ነው ብለዋል ።

የቁፋሮና ጠረጋ ስራው የማምረቻ ቦታን በመለየት በመጪው የፈረንጆች ዓመት ወርቅ ለማምረት ያስችላልም ብለዋል።

ኩባንያው ከዚህ ጎን ለጎን ለቀጣይ ስራው የሚረዱት ባለሙያዎችን ከአካባቢው ነዋሪዎች የመመልመልና የማሰልጠን ስራ እየሰራ መሆኑን ዋና ስራ አስፍጻሚው ተናግረዋል።

በብሩክ ያሬድ
2022-10-27