
በጎርጎሮሲያውኑ አቆጣጠር በዚህ ዓመት በአፍሪካ የዋጋ ግሽበቱ 13.5 በመቶ ከፍ ሊል እንደሚል ተነገረ። 20 የአፍሪካ ሀገራት ደግሞ ያልከፈሉት ከፍተኛ የብድር ዕዳ አለባቸው ተብሏል።
ከሰሀራ በታች ባሉ የአህጉሪቱ ክፍል ያሉ ሀገራት ያለባቸው የብድር ጫና ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርታቸው 60% እንደሚይዝ ተሰምቷል።
በተጨማሪ 40% የሚሆኑት የአካባቢው ሀገራት ደግሞ ባለሁለት አሃዝ የዋጋ ግሽበት እያጋጠማቸው ነው። በመሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላይ የሚታየው የዋጋ ጨማሪ ግሽበቱን እንዳባሰው ነው የተዘገበው።
መንግሥታት ገቢያቸውን ለማሳደግ የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲያሰፉ ባለሙያዎች እያሳሰቡ ነው ይገኛሉ። በአህጉሪቱ በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሻለ አቅም አላቸው የሚባሉ ሀገራት አሁን ላይ ትልቅ ፈተና ውስጥ ስለመግባታቸው አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል።
እንደአብነት በናይጄሪያ የንግዱ ሁኔታ አስተማማኝ ያልኾነ ከዚያ ይልቅ ተስፋ አስቆራጭ መኾኑ ተነግሯል። ይህን ያገናዘበ ለውጥ ባለመደረጉ እንዲሁም ያለው ውስን የኾነ መሠረተ ልማት በመኾኑ በሀገሪቱ ያሉ ኢንዱስትሪዎች ለችግራቸው መፍትሔ እንዲሰጥ መንግሥታቸውን እየጠየቁ ይገኛሉ።
በሌሎችም የአፍሪካ ሀገራት በተለይም የኢንዱስትሪ ዘርፉ በምጣኔሀብታቸው ላይ ጉልህ ሚና በሚያሳርፍበት የኃይል መቆራረጥ፣ የመሠረተ ልማት አለመሟላት እንዲሁም የፋይናንስ አሊያም የውጪ ምንዛሬ በሚፈልጉት መጠን አለማግኘታቸው በሀገራቱ ምጣኔ ሀብት ላይ ከባድ አደጋን ጋርጧል።
እነዚህ ችግሮች ሌሎች አዳዲስ የንግድ ዘርፎች ገበያዉን እንዳይቀላቀሉ ሳንካ እንደኾነም ተሰምቷል።
ከዚህ በፊት አዲሱ የኬኒያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ “የዕዳ ክፍያ ጫና በአህጉሪቱ የተገኘውን የእድገት እንዳልነበረ ሊያደርገው ይችላልና ለአፍሪካ ሀገራት የዕዳ ስረዛ እንዲደረግ መጠየቃቸው የሚታወስ ነው።
በሙሉጌታ በላይ
2022-10-28