ኢትዮጵያና የአለም ባንክ የ400 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
በስምምነቱ ከተፈረመው 400 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 350 ሚሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ ሲሆን 50 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ብድር መሆኑ ታውቋል፡፡
የፋይናንስ ድጋፉ የትምህርትን ጥራትንና ውጤታማነትን ለማሻሻልና የስርዓተ ምግብን አገልግሎት ለማጎልበት የሚውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና በአለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ተጠሪ የሆኑት ሚስተር ኦስማን ዲዮን ተፈራርመዋል፡፡
በብሩክታዊት አስራት
2023-07-27