
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የአሜሪካን የደህንነት ማስጠንቀቂያ ነቀፉ።
ፕሬዝዳንቱ የአሜሪካ ኢምባሲ በጆሃንስበርግ ከተማ የሽብር ጥቃት ይፈጸማል ሲል ማስጠንቀቁን ነው የነቀፉት። የአሜሪካ ኢምባሲ ሳያማክረን ጥቃት ሊፈጸም ይችላል ማለቱ ተገቢ አይደለም ብለዋል።
ኢምባሲው በጆሃንስበርግ የንግድ እንቅስቃሴ እና የፋይናንስ ተቅቋማት ባሉበት በሳንድተን በሳምንቱ መጨረሻ የሽብር ጥቃት ሊፈጸም ይችላል ሲል በድረገጹ አስታውቋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-10-28