ኤለን መስክ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የሆነውን ትዊተርን በይፋ በእጁ አስገባ። ከዓለማችን ባለጸጎች አንዱ መስክ ትዊተርን የመግዛት ስምምነቱን የፈጸመው በ44 ቢሊዮን ዶላር ነው።
ቀድሞ ትዊተርን የመግዛት ድርድሩ ያልተሳካለት የቴስላ ቴክኖሎጂ ተቋም ዋና ኃላፊ መስክ አሁን ላይ ትዊተርን የመግዛት የመጨረሻ ስምምነቱን አድርጓል።
የማህበራዊ ትስስር ገጹን ከተቆጣጠረ በኋላ ሶስት የተቋሙ ባለስልጣናትን የቀድሞውን ዋና ኃላፊ ፓራግ አግራዋልን ጨምሮ ከስራ ማባረሩም ተገልጿል።
መስክ በትዊተር ገጹም የማህበራዊ ትስስር ገጹን ምልክት በሚገልጽ መንገድ ወፏ ነጻ ወጣች ብሏል።
በብሩክ ያሬድ
2022-10-28
