ሀገሬ ቲቪ

አሜሪካ ከታይዋን ጋር ማበሯን ታቁም ስትል ቻይና አሳሰበች

አሜሪካ ከታይዋን ጋር የምታደርገውን ምስጢራዊና ህገ ወጥ ትብብር ልታቆም ይገባል ሲሉ የቻይናው ማዕከላዊ ጦር ኮሚሽን ምክትል አዛዥ ጀነራል ዣንግ ዩዢያ ተናግረዋል።

ጄነራሉ ይህን ያሉት በቻይና ጉብኝት እያደረጉ ከሚገኙት የአሜሪካው ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ጋር ዉይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

ጀነራል ዣንግ አክለው፤ ታይዋንን ከእናት ሀገሯ ቻይና ጋር ማዋሃድ የቻይና ጦር ተልዕኮና ኃላፊነት ነው ብለዋል። የደህንነት አማካሪዉን ጉዞ ተከትሎ ኋይት ሃውስ በተሰጠችው መግለጫ መሰረት፤ በቀጣዩ ሳምንት ፕሬዝዳንት ባይደን እና የቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ በስልክ እንደሚወያዩ አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።

በበላይሁን ፍሰሃ
2024-08-29