ሀገሬ ቲቪ

ስፔን በምዕራብ አፍሪካ ያላትን ፖሊሲ ልታድስ ነው

የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ፣ ሀገራቸው በመጪዎቹ ሳምንታት ከአፍሪካ ጋር ለምታደርገው ግንኙነት አዲስ ስትራቴጂ እንደሚያጸድቁ ተነገረዋል።

የምዕራብ አፍሪካና የሳህል ቀጣና ቅድሚያ እንደሚሰጣቸውም ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል።

በምዕራብ አፍሪካ ጉብኘት እያደረጉ የሚገኙት ፕሬዘዳንቱ ከምዕራብ አፍሪካ የሚነሱ ህገ ወጥ ፍልሰትኞች ለደህንነት ስጋትን ደቅነዋል፣ ለዚህ ጠበቅ ያለ የደህንነት ህግ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

የስፔን መንግስት ህገ ወጥ ፍልሰትኞችን ለመከላከል፣ ከምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ጋር በጥብቅ እንደሚሰራም ገልፀዋል። ፕሬዝዳንቱ በቀጣይ በሞሪታንያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በወንድማገኝ አበበ
2024-08-29