
በእስራኤል እና ሂዝቦላህ መካከል ያለው ውጥረት መባባሱን ተከትሎ፤ አሜሪካ ተጨማሪ ወታደሮቿን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ልካለች።
የፔንታጎኑ ቃል አቀባይ ሜጀር ጀነራል ፓት ሬይደር እንዳስታወቁት፤ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ከፍ ማለቱን ተከትሎ በቀጠናው ከሚገኘው ጦር ተጨማሪ ወታደሮችን ልከናል ብለዋል።
አዲስ የተላኩት ወታደሮች ቁጥር ምን ያህል ስለመሆኑ የተነገረ ነገር ባይኖርም፤ አሜሪካ ከዚህ በፊት 40 ሺህ ወታደሮችን በቀጠናው ስለማሰማራቷ ኣናዶሉ ዘግቧል።
እስራኤል ሂዝቦላህን ኢላማ ያደረጉ ናቸው ያለቻቸውን ጥቃቶች አጠናክራ በቀጠለችበት በዚህ ጊዜ፤ 356 ሊባኖሳዊያን መሞታቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት እየገለጹ ይገኛሉ።
በአስናቀ ማናዬ
2024-09-24